ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤
ኢሳይያስ 57:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በባሉጥ ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባሉጥ ዛፎች መካከል፣ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሥር በዝሙት የምትቃጠሉ፣ በሸለቆዎች፣ በዐለት ስንጣቂዎችም ውስጥ ልጆቻችሁን የምትሠዉ አይደላችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በዋርካ ዛፎች መካከልና በየለምለሙ ዛፍ ሥር በፍትወት የምትቃጠሉ ናችሁ፤ እንዲሁም በሸለቆዎች ውስጥ በቋጥኞች መካከል ልጆቻችሁን ለዕርድ ታቀርባላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣዖት ደስ የምትሰኙ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ልጆቻችሁን የምትሠዉ፥ እናንተ የጥፋት ልጆችና የዐመፀኞች ዘሮች አይደላችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፥ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን? |
ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤
ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በማሳዘናቸው ነበር፤ ይኸውም ለባዕዳን አማልክት ሰገዱ፤
ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በአምላክሽ በጌታ ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ድምፄንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ብቻ እወቂ ይላል ጌታ።
ጌታም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ “ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም አመነዘረች።
ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት፥ ይህን ርኩሰት እንዲያደርጉ ባላዛቸውም በልቤም ባላስበውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሌክ በእሳት ለመሠዋት፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።
ባቢሎን በጌታ እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከወይን ጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እንደ እብድ ሆነዋል።
እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያሉትን የቶፌት መስገጃዎችን ሠረተዋል።
እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቆጣኝን ቁርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቁርባናቸውን አፈሰሱ።
ቁርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤
ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፥ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ ከለመለመውም ዛፍ ሁሉ ሥርና ቅጠሉም ከበዛ ባሉጥ ሁሉ ሥር ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ባቀረቡበት ስፍራ በወደቁ ጊዜ ያኔ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እነሆም፥ ከእስራኤል ልጆች አንዱ መጥቶ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ እያለቀሱ ሳሉ በእነርሱ ፊት ምድያማዊት የሆነችን አንዲት ሴት ወደ ወንድሞቹ አመጣት።
ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረጅሙ ተራሮች፥ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።
አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቁጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴስነዋልና፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሣ ሀብታሞች ሆነዋልና፤” ብሎ ጮኸ።