ኢሳይያስ 48:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ስሜ ስል ቍጣዬን አዘገያለሁ፤ ስለ ምስጋናዬም ስል ከአንተ እገታዋለሁ፤ ይኸውም እንዳልቈርጥህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለ ስሜ ክብር ቊጣዬን አዘገያለሁ፤ ሰዎችም ያመሰግኑኝ ዘንድ ቊጣዬ እንዳያጠፋችሁ እገታዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ስሜ ቍጣዬን አሳይሃለሁ፤ እንዳላጠፋህም ግርማዬን አመጣብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምሥጋናዬ እታገሣለሁ። |
ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።
የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።