Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 48:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ፤ ስለምን ስሜ ይነቀፋል? ክብሬን ለሌላ አልሰጥም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስለ ራሴ፣ ስለ ራሴ ስል አደርጋለሁ፤ ራሴን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ? ክብሬን ለማንም አልሰጥም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለ እኔ ስለ ራሴ ይህን አደርገዋለሁ፤ ስሜስ ለምን ይነቀፋል? ክብሬንም ለማንም አልሰጥም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ ይህን ለአ​ንተ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ስሜ ተነ​ቅ​ፎ​አ​ልና፤ ክብ​ሬ​ንም ለሌላ አል​ሰ​ጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ ስሜ ተነቅፎአልና፥ ክብሬን ለሌላ አልሰጥም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 48:11
23 Referencias Cruzadas  

ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ አዳናቸው።


ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ።


አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።


የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፥ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።


ስለ እኔም ስለ አገልጋዬም ዳዊት ይህችን ከተማ አድናታለሁ፥ እጋርዳታለሁም።”


እኔ ጌታ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።


መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም አላስብም።


ስለዚህ፥ አንተ፦ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር፥ ከመሆኑም በፊት አሳይቼህ ነበር።


ስለ ስሜ ቁጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳለጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።


ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል ጌታ፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል ጌታ፥ ስሜም ያለማቋረጥ በየእለቱ ቀኑን ሙሉ ይሰደባል።


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።


የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ የምሠራው ስለ እናንተ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው በመንግሥታት መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው።


ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።


ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በሕዝቦች መካከል ይሰደባልና” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


ጌታ የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ጌታ ሕዝቡን አይተውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos