Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ነገር ግን ከመካከላቸው ሳወጣቸው ባዩ አሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስለ ስሜ ተቈጠብሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር መርቼ ሳወጣ በተመለከቱኝ ሕዝቦች ፊት ስሜ እንዳይነቀፍ ይህን ሁሉ አላደረግሁም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን በፊ​ታ​ቸው ባወ​ጣ​ኋ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ፊት ከሁሉ በላይ የሚ​ሆን ስሜን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ አደ​ረ​ግሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 20:14
9 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በመካከላቸው ባሉ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


ይኸውም በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ደግሞ ለክብሩ ምስጋና እንድንሆን ነው።


በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ።


ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ፤ ስለምን ስሜ ይነቀፋል? ክብሬን ለሌላ አልሰጥም።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው የምድር ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ወደ ሰጠኋቸው ምድር አላመጣቸውም ብዬ በምድረ በዳ ማልሁባቸው።


ቅዱሱ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፥ ቅዱሱ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ እንዲሰደብ አልፈቅድም፤ አሕዛብም በእስራኤል ያለሁ ቅዱስ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios