ኢሳይያስ 40:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጕልበት ይጨምራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለደከሙት ብርታትን ይሰጣል፤ ለዛሉትም ኀይልን ይጨምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደካሞች ኀይልን ይሰጣል፤ መከራ የሚቀበሉትንም አያሳዝናቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደካማ ኃይልን ይሰጣል ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። |
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።
እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውኃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬሸ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል።