Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 50:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 50:4
31 Referencias Cruzadas  

ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጉልበት ታጸና ነበር።


ማለዳ ጮኽሁ፥ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።


አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን አሰማኝ፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳውቀኝ።


መሥዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም፥ የሚሰማ ጆሮ ሰጠኸኝ፥ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም።


ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።


የጩኸቴን ድምፅ አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።


ድንቅ ሥራህ በጨለማ፥ ጽድቅህም በሚረሳበት ምድር ትታወቃለችን?


ሰውን የልቡ ኀዘን ያዋርደዋል፥ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።


ሰው በአፉ መልስ ደስ ይለዋል፥ ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!


በአግባብ የተነገረ ቃል፥ በብር ፃሕል ላይ እንደተቀመጠ ወርቅ ነው።


ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ እለት ከእለት፥ ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ ወሬውንም መስማት ፍርሃት ያሳድራል።


“እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?”


በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዐይን ይበራል፤ የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል።


ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።


ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?


ልጆችሽም ሁሉ ከጌታ የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።


ምስክርነቱን አሽገው፤ ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው።


ጌታም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እንዲህም አለኝ፦ “እነሆ፥ ቃሎቼን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤


የደከመችውን ነፍስ አርክቻለሁና፥ የዛለችውንም ነፍስ ሁሉ አጥግቤአለሁና።”


በየዕለቱም ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት በግ ጠቦት ለጌታ ያቅርብ፤ ማለዳ ማለዳም ያቅርበው።


እናንተ ደካሞችና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ በምኵራባቸው ያስተምራቸው ነበር፥ ተገርመውም እንዲህም አሉ “ይህን ጥበብና ኃይል ከየት አገኘው?


አንድም ቃል እንኳ ሊመልስለት የቻለ ማንም አልነበረም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድስ እንኳ አልነበረም።


ተቃዋሚዎቻችሁ በሙሉ ሊቃወሙትና ሊከራከሩት የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።


ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።


ዘቦቹም “እንደዚህ ሰው ማንም ከቶ አልተናገረም፤” ብለው መለሱ።


ጌታ እንዲህ አለኝ፤ ‘የተናገሩት መልካም ነው፤


ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos