Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 68:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አቤቱ፥ የተትረፈረፈ ዝናብ ለርስትህ አዘነብህ፥ በደከመም ጊዜ አንተ አጸናኸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 መንጋህ መኖሪያው አደረጋት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከበረከትህ ለድኾች ሰጠህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሕዝቦችህም መኖሪያቸውን በዚያ አደረጉ፤ በቸርነትህም ለድኾች የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አዘጋጀህላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሰው​ነ​ቴን በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፥ ስድ​ብ​ንም ሆነ​ብኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:10
18 Referencias Cruzadas  

አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።


ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፥ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፥ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።


ትልምዋን ታረካለህ፥ ቦይዋንም ታስተካክላለህ፥ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።


ከተኣምራትህ የተነሣ በምድር ዳርቻ የሚኖሩ ይፈራሉ፥ የጥዋትንና የማታን መውጫዎች ደስ ታሰኛቸዋለህ።


የምትገዛልህን እርግብ ለአራዊት አትስጣት፥ የችግረኞችህን ነፍስ መቼውንም አትርሳ።


ዓለቱን መታ፥ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፥ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን?”


ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።


በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ ጌታም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችሁታል፤ በጌታም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?”


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤


የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ሀብታሞችን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።


አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።


በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው ለመንጋው መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በኃይል በመግዛት አይሁን።


ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos