የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ኢሳይያስ 37:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፥ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ። |
የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።
የሦስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠላቶችህ ሰይፍ እንዲያገኝህ ከጠላቶችህም ፊት እንድትሰደድ፥ ወይም ሦስት ቀን የጌታ ሰይፍ ቸነፈርም በምድር ላይ እንዲሆን፥ የጌታም መልአክ በእስራኤል ምድር ሁሉ ጥፋትን እንዲያመጣ ምረጥ፤’ ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አሁን ወስን።”
ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የጌታ መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
ጌታ ግብጽን ሊመታ ያልፋል፤ ደሙንም በጉበኖቹና በሁለቱ መቃኖች ላይ ያያል፥ ጌታም በበሩ ያልፋል፥ አጥፊውም ሊመታችሁ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይፈቅድም።
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፤ እንዲህ ይላል የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።
የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።
ፈረሰኛው ይጋልባል፥ ሰይፍ ይንቦገቦጋል፥ ጦር ይብለጨለጫል የተገደለ ብዛት፥ የበድን ክምር፥ ሬሳው ማለቂያ የለውም፤ በሬሳቸውም ይሰናከላሉ።