ኢሳይያስ 37:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ ጌታ ሆይ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ለመገዳደር የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤቱ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህን ክፈትና እይ። ሰናክሬም ሕያው አምላክን ለመሳደብ የላከውን ቃል ሁሉ ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሰናክሬም! እንዴት አድርጎ አንተን ሕያው አምላክን እንደ ዘለፈ ተመልከት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፥ አቤቱ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ፥ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ስማ። |
አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ አለቃው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ ጌታ ሰምቶ እንደሆነ፥ አምላክህ ጌታም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደሆን፥ ስለዚህ አንተም በሕይወት ስለተረፉት ቅሬታ ጸልይ አሉት።”