ኢሳይያስ 34:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም ለክታ ከፈለችላቸው፤ ለዘለዓለም የእነርሱ ትሆናለች፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይኖሩባታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤ እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች። ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እያንዳንዳቸው የት መኖር እንደሚገባቸው ወሰነ፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ ለዘለዓለም ይኖሩበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፤ እጁም ከፈለችላቸው፤ ለዘለዓለም ይሰማሩባታል፤ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይወርሱአታል፤ በውስጥዋም ያርፉባታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፥ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፥ ለዘላለም ይገዙአታል፥ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል። |
ሕዝቦች እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፤ እርሱ ግን ይገሥጻቸዋል፤ እነርሱም እየሸሹ ይርቃሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ በነፋስ ፊት፥ ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረውም ትቢያ ይበተናሉ።
በሌሊትና በቀንም አትጠፋም፤ ጢስዋም ለዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘለዓለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።
ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ተመልክተው ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ሂዱ፥ ምድሩንም ዞራችሁ እዩና ጻፉት፥ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በጌታ ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።”