ኢሳይያስ 33:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራ ጎዳናዎች ባድማ ሆኑ፥ መንገዶችም የሚያልፍባቸው ጠፋ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ፥ ሰውንም አልተመለከተም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውራ ጐዳናዎች ባዶ ናቸው፤ በመንገድ ላይ ሰው የለም፤ ስምምነቱ ፈርሷል፤ መካሪዎቹ ተንቀዋል፤ የሚከበርም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አውራ ጐዳናዎች ባዶ ሆኑ፤ በመንገዶቹ ላይ ተጓዦች የሉም፤ ቃል ኪዳን ፈረሰ፤ የውል ስምምነቶች ተጥሰዋል፤ ከዚህም የተነሣ ምክር የሚሰጠው ሰው አልተገኘም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ የአሕዛብም መፈራት ቀረ፤ ቃል ኪዳናቸውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አልተመለከታቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዶች ባድማ ሆኑ፥ ተላላፊም ቀረ፥ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም። |
በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፥ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፥ ድንግሎችዋም ተጨነቁ እርሷም በምሬት አለች።
በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።
ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።