ኢሳይያስ 29:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላቸው የእጄ ሥራ የሆኑ፣ ልጆቻቸውን ሲያዩ፣ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብን ቅዱስ ቅድስና ያውቃሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሀት ይቆማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቻቸውን በመካከላቸው ባዩ ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ ያከብራሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሃት ይቆማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ልጆቻቸው የእጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፥ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ |
ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም።
ምድርን እንደሚሸፍን ደመና በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፥ በአንተ በኩል ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ፥ አሕዛብ እንዲያውቁኝ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።
ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።
ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።