ኢሳይያስ 24:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባድማ የሆነችው ከተማ ፈረሰች፤ ማንም እንዳይገባበት የሁሉም ቤት ተዘጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈራረሰችው ከተማ ባድማ ሆነች፤ የየቤቱም መግቢያ ተዘጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፈረሰችው ከተማ ባድማ ትሆናለች፤ ማንም ሰው እንዳይገባበት ቤቱ ሁሉ ተዘግቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሞች ሁሉ ምድረ በዳ ሆኑ፤ ቤቶችም ሁሉ ማንም እንዳይገባባቸው ተዘጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባድማ የሆነችው ከተማ ፈረሰች፥ ማንም እንዳይገባበት ተዘጋ። |
የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።
ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፥ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፥ የኀጥኣንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ደግማም አትገነባም።
የተመሸገችው ከተማ ብቻዋን ሆነች፤ እንደ ምድረ በዳ ሆና የተተወች መኖሪያ ሆናለች፤ በዚያም ጥጃ ይሰማራል፥ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወታደሮቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በነበረው በር በኩል ከከተማይቱ ወጡ፤ መንገዳቸውንም ወደ ዓረባ አድርገው ተጓዙ።
የከተማይቱም ቅጥር ተጣሰ፥ ወታደሮችም ሁሉ ሸሹ፥ በሁለቱም ቅጥሮች መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ዓረባም በሚወስደው መንገድ ሄዱ።
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጡ፤ ንጉሣቸው በፊታቸው ሄዷል፥ ጌታም በራሳቸው ላይ ነው።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤