ኢሳይያስ 20:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፥ ‘እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘እኛን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያድኑናል ብለን ተስፋ ያደረግንባቸውና ወደ እነርሱ የተጠጋንባቸው አገሮች ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እኛማ እንዴት እናመልጣለን?’ ” ይላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን በዚች ደሴት የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ለርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ ከአሦር ንጉሥ ራሳቸውን ያላዳኑ እኛን እንዴት ያድኑናል?” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፥ እኛስ እንዴት እናመልጣለን? ይላሉ። |
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
አንቺም የተደመሰስሽ ሆይ! ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዓይንሽንም በኩል ተኩለሽ በተቆነጀሽ ጊዜ፥ በከንቱ እራስሽን ታጌጫለሽ፤ ውሽሞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና።
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ ይህንኑ አረጋግጠውልናል።