ኢሳይያስ 19:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተነደፈ የተልባ እግር ለሚፈትሉ፥ የተባዘተ ጥጥ የሚሰሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቆርጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተነደፈ የተልባ እግር የሚፈትሉ፣ የተባዘተ ጥጥ የሚሠሩ ሸማኔዎችም ተስፋ ይቈርጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተበጠረውን የተልባ እግር የሚሠሩ ተስፋ ይቈርጣሉ ቀጭን ሐር የሚሠሩ ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቈራረጠውንም መረብ የሚጠግኑ፥ ነጩንም ልብስ የሚሠሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተበጠረውንም የተልባ እግር የሚሠሩ፥ ነጩንም ልብስ የሚሰሩ ሸማኔዎች ያፍራሉ። |
ሁለቱ ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹም ላይ የነበሩትን ማቶቶች የሚመስሉ ጉልላቶች፥ በምሰሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑት ሁለቱ መረቦች።
ዓላማ ሆኖ እንዲያገለግልሽ፥ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሻ ደሴቶች የመጣ ሰማያዊና የወይን ጠጅ ነበር።