ኢሳይያስ 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን እስራኤል፤ ከግብጽና ከአሦር ጋር የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እስራኤል፣ ከግብጽና ከአሦር ጋራ የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እስራኤል ከግብጽና ከአሦር ጋር ተደምራ ሦስተኛ አገር ትሆናለች፤ እነዚህም ሦስት ሕዝቦች በዓለም መካከል በረከት ይሆናሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ወራት እስራኤል ለግብፅና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፤ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦ ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥ ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል። |
በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራዊያንም ወደ ግብጽ፥ ግብፃዊውም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብፃውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በዕቅፋቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፥ “በረከት በእርሷ ላይ አለና አታጥፉት” እንደሚባለው፥ ሁሉን እንዳላጠፋ ስለ አገልጋዮቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆም፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጉልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሏችኋል።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ በረከት መሆን እንድትችሉ አድናችኋለሁ፤ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
ተደስተዋልና የእነርሱ ባለ ዕዳዎች ናቸው፤ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገር አሕዛብ ተካፋዮች ከሆኑ በሥጋዊ ነገር ደግሞ ሊያገለግሉአቸው ይገባቸዋል።
“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”