Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ይህም የአብርሃም በረከት፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አሕዛብ እንዲደርስና የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለአብርሃም የተሰጠው በረከት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ለአሕዛብ እንዲደርስ ዋጅቶናል፤ ይኸውም በእምነት የመንፈስን ተስፋ እንድንቀበል ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኛ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነን የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ እን​ድ​ና​ገኝ የአ​ብ​ር​ሃም በረ​ከት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለስ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 3:14
48 Referencias Cruzadas  

አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።


በእርሱም አማካኝነት ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት እንችላለን።


ከእናንተ ይህን ብቻ መማር እፈልጋለሁ፤ መንፈስን የተቀበላችሁት በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማት?


ስለዚህ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ከአብ ተቀብሎ ይህን እናንተ አሁን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።


አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ አዲስ መንፈስም በውስጣቸው አኖራለሁ፥ ከሥጋቸውም የድንጋዩን ልብ አወጣለሁ፥ የሥጋንም ልብ እሰጣቸዋለሁ፤


ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ ለወንድማማች እውነተኛ ፍቅር፥ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ይህንንም በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።


መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፥ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፥ ፍሬያማውም እርሻ ዱር ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይህ ይሆናል።


ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።


እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን፥ በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ እጸልያለሁ፤


በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።


ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር “አባ አባት” ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።


የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።


ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።


እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።


እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው።”


መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”


እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በዚህች ከተማ ቆዩ።”


እንግዲያውስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው!”


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሰውርም፥ መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ጌታ የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።


አገልጋዬ እስራኤል፥ የመረጥኩህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥


ቃሌን ሰምተሃልና፥ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ።”


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios