የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ?
ኢሳይያስ 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፎስም አለቆች ተታለዋል፤ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑት ግብጽን አስተዋታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጣኔዎስ አለቆች ተሞኝተዋል፤ የሜምፊስ ሹማምት ተታልለዋል፤ የሕዝቧ ዋና ዋናዎች፣ ግብጽን አስተዋታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጾዓን ባለ ሥልጣኖች ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ መሪዎችም ተታለሉ፤ የሕዝብዋ ከፍተኛ አማካሪዎች ግብጽን አሳትዋት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጣኔዎስ አለቆች አለቁ፤ የሜምፎስም አለቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብፃውያን በየወገናቸው ተሳሳቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጣኔዎስ አለቆች ሰነፎች ሆነዋል፥ የሜምፎስም አለቆች ተሸንግለዋል፥ የነገዶችዋ የማዕዘን ድንጋዮች የሆኑ ግብጽን አሳቱ። |
የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ?
በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።
አንቺ በግብጽ የምትቀመጪ ሴት ልጅ ሆይ! ሜምፎስ ባድማ ትሆናለችና፥ ትቃጠላለችምና፥ የሚቀመጥባትም አይገኝምና በምርኮ ስለምትሄጂ ዕቃዎችሽን አሰናጂ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አስወግዳለሁ፥ ምስሎችንም ከኖፍ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከግብጽ ምድር ገዢ አይነሳም፥ በግብጽ ምድር ላይ ፍርሃትን አኖራለሁ።
እነሆ፥ ከጥፋት ሸሽተው ቢሄዱ እንኳ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች፤ ሳማም የብራቸውን ጌጥ ይወርሰዋል፥ እሾኽም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤልም በትረ መንግሥት ይነሣል፥ የሞዓብንም ግንባር ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።