እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
ኢሳይያስ 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፤ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፣ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን ከወርቅ ይልቅ፥ ከኦፌር ወርቅም የበለጠ ብርቅና ውድ አደርገዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተረፉትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፤ ሰውም ከሰንፔር ዕንቍ ይልቅ የከበረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፥ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል። |
እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።
በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።
እኔም፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፤ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፤ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፤ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤