Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 13:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሰውን ከወርቅ ይልቅ፥ ከኦፌር ወርቅም የበለጠ ብርቅና ውድ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፣ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፤ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የተ​ረ​ፉ​ትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከ​በሩ ይሆ​ናሉ፤ ሰውም ከሰ​ን​ፔር ዕንቍ ይልቅ የከ​በረ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፥ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 13:12
11 Referencias Cruzadas  

እነርሱም በመርከብ ተጒዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ ከዐሥራ አራት ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ይዘውለት መጡ።


ኦፊርን፥ ሐዊላና ዮባብን ወለደ። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።


ጥበብ ኦፊር ከሚባል ወርቅና፥ መረግድና ሰንፔር ከሚባሉ ዕንቆች የከበረች ናት።


ሕፃናት ልጆችሽን እያነሣ በአለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተባረከ ነው።


በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።


በደን ውስጥ የሚቀሩትም ዛፎች በቊጥር ያነሱ ከመሆናቸው የተነሣ ሕፃን ልጅ እንኳ ሊቈጥራቸው ይችላል።


ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።


በዚያን ጊዜ ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው “በምግብም ሆነ በልብስ ራሳችንን ችለን እንተዳደራለን፤ ‘ባል የላቸውም’ ተብለን ከመሰደብ እንድንድን የአንተ ሚስቶች ተብለን እንድንጠራ ብቻ ፍቀድልን” ብለው ይለምኑታል።


እኔም “አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። እርሱም “ከተሞች እስኪፈርሱ፥ ቤቶችም የሚኖርባቸው አጥተው ወና እስኪሆኑና አገሪቱም የተፈታች ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው።


ሕዝቡን ወደ ሩቅ አገር እሰዳለሁ፤ አገሪቱም ባድማ ትሆናለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos