ኢሳይያስ 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፤ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱ ዕቅድ ግን ይህ አይደለም፤ ይህም ጉዳይ በሐሳባቸው ውስጥ የለም፤ የእነርሱ ዓላማ ግን ጥቂቶቹን ሳይሆን ብዙዎችን ሕዝቦች ለማጥፋት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በልቡ እንዲህ አይመስለውም፤ እንዲህም አያስብም፤ ነገር ግን ማጥፋት፥ ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብ መቍረጥ በልቡ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ እንዲሁ አያስብም፥ በልቡም እንዲህ አይመስለውም፥ ነገር ግን ማጥፋት፥ ጥቂት ያይደሉትንም አሕዛብን መቍረጥ በልቡ አለ። |
እነሆ፥ የከለዳውያን አገር! ይህ ሕዝብ ሆኖ አይገኝም፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል፤ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፥ ባድማም አደረጓት።