ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
ኢሳይያስ 1:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮን በፍትሕ፤ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽዮን በፍትሕ፣ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እውነተኛ ስለ ሆነ ጽዮንን በፍርድ ያድናታል፤ በውስጥዋ ከሚኖሩት መካከል ንስሓ የሚገቡትን ይታደጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምርኮኞችሽ በእውነትና በምጽዋት ይድናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽዮን በፍርድ ከእርሷም የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ። |
ጌታም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፥ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላላም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
ሕዝቤ ሆይ፥ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደውን፥ የቤዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፥ የጌታን ጽድቅ እንድታውቅ ከሺጢም ጀምሮ እስከ ጌልገላ ድረስ የሆነውን እባክህን አስታውስ።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።