Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 35:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አንበሳም አይኖርበትም፥ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፥ እነዚህ ከዚያ አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አንበሳ አይኖርበትም፤ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤ እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤ የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አንበሶችም ሆነ ነጣቂ አውሬዎች በዚያ አይገኙም፤ በዚያ መንገድ የሚመላለሱ እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች ብቻ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አን​በሳ አይ​ኖ​ር​በ​ትም፤ ክፉ አው​ሬም አይ​ወ​ጣ​በ​ትም፤ በዚ​ያም አይ​ገ​ኙም፤ የዳ​ኑት ግን በዚያ ይሄ​ዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አንበሳም አይኖርበትም፥ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፥ ከዚያም አይገኙም፥ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 35:9
23 Referencias Cruzadas  

“ጌታ የተቤዣቸው፥ የተቀደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፥ “የተፈለገች፥ ያልተተወችም ከተማ” ትባያለሽ።


“በዚያ ቀን፦ ‘ባሌ’ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ፦ ‘በኣሌ’ ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል ጌታ፤


ከእነርሱ ጋር የሰላምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፥ ክፉ አራዊትን ከምድሪቱ አጠፋለሁ፤ በሰላምም በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ።


ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ።


የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


ጌታ የታደጋቸው፥ ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።


በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።


በታማኝ ኪዳንህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራሃቸው፤ በኃይልህ ወደ ቅድስናህ ማደሪያ አስገባሃቸው።


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ፥ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ አይደለም፤


መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና


ጽዮን በፍትሕ፤ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።


ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።


ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ “መንገዷ ይህች ናት በእርሷም ሂድ” የሚለውን ቃል ይሰማሉ።


ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅከው፥ የዳኑትም እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?


“አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል ጌታ፥ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረኩበት አገር አድናለሁና፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፋልም በደኅንነትም ይቀመጣል፤ እርሱንም ማንም አያስፈራራውም።


እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።


እለፉ፥ በበሮች በኩል እለፉ፤ የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፥ ጎዳናውን አዘጋጁ፥ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓርማ አሳዩ።


የሜዳ ዛፍም ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በምድራቸውም በሰላም ይኖራሉ፤ የቀንበራቸውንም ዘንግ ስሰብር ከሚገዙአቸውም እጅ ሳድናቸው፥ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios