ሆሴዕ 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ብታመነዝር እንኳ እስራኤል ሆይ! ይሁዳ በደለኛ አይሁን፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ!” ብላችሁም አትማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣ ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ። “ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብላችሁም አትማሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እናንተ ብታመነዝሩም እንኳ የይሁዳ ሕዝብ በደለኛ እንዲሆን አታድርጉ፤ ወደ ጌልጌላ ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ሆይ፥ አንተ ብታመነዝር ይሁዳ አይበድል፥ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብላችሁ አትማሉ። |
ዳግምም በይሁዳ ተራሮች ላይ በከፍታ ላይ የሚገኙ የማምለኪያ ሥፍራዎችን ሠራ፥ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን እንዲያመነዝሩ አደረጋቸው፥ ይሁዳንም አሳተው።
እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በጌታ ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥
ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ።
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።
የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።
በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።”
ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ሳሉ ጠላኋቸው፤ ስለ ሥራዎቻቸውም ክፋት ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።
“የእስራኤል ልጆች ሆይ! ይህን ወድዳችኋልና ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላ ኑና ኃጢአትን አብዙ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን አሥራታችሁን አምጡ፤
የሞተውን ሰው የሚያቃጥለው ዘመዱ አጥንቱን ከቤቱ አንስቶት ባወጣው ጊዜ፥ በቤቱም በውስጠኛው ክፍል ያለውን፦ “በእዚያ እስከ አሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሰው አለን?” ይለዋል፥ እርሱም፦ “ማንም የለም” ይላል፤ ያንጊዜ፦ “የጌታን ስም ልንጠራ አይገባንምና ዝም በል” ይለዋል።
አሺማ በምትባል የሰማርያ ጣኦት የሚምሉና፦ ‘ዳን ሆይ! ሕያው አምላክህን!’ ደግሞ፦ ‘ሕያው የቤርሳቤህን መንገድ!’ ብለው የሚምሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ዳግመኛም አይነሡም።”
ጌታም ኢያሱን፦ “ዛሬ የግብጽን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።
ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ላከ፤ እንዲህም አላቸው፦ “ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ፤” ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።