ሆሴዕ 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣ የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤ እሾኽና አሜከላ ይበቅልባቸዋል፤ መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤ በዚያ ጊዜ ተራሮችን፣ “ውደቁብን!” ኰረብቶችንም፣ “ሸፍኑን!” ይላሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የእስራኤል ሕዝብ አዌን በተባለ ከተማ ጣዖት በማምለክ ኃጢአት የሚሠሩባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ይፈራርሳሉ፤ በመሠዊያዎቻቸውም ላይ እሾኽና አሜከላ ይበቅሉባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ተራራዎችን “ደብቁን!” ኮረብቶችንም “ጋርዱን!” ይላሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ እሾህና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፥ ተራሮችንም፦ ክደኑን፥ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን ይሉአቸዋል። Ver Capítulo |