ሆሴዕ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ደግሞ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ እንዲሆን ወደ አሦር ተማርኮ ይወሰዳል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ ወደ አሦር ይወሰዳል፤ ኤፍሬም ይዋረዳል፤ እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣዖቱ ወደ አሦር በመወሰድ ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ሆኖ ይቀርባል፤ እስራኤል ከተከተለው ክፉ ምክር የተነሣ ኀፍረትና ውርደት ይደርስበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስረው ወደ አሦር ይወስዱታል፤ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፤ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለንጉሡ ለኢያሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ ወደ አሦር ይማረካል፥ ኤፍሬምን እፍረት ይይዘዋል፥ እስራኤልም በምክሩ ያፍራል። |
ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።
የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።