ዕብራውያን 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀደም ብሎ የምሥራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ምክንያት ስላልገቡ፥ እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ተጠብቆላቸዋል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዕረፍቱ ገና የሚገቡ አንዳንዶች አሉ፤ ቀድሞ የምሥራቹ ቃል የተሰበከላቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍት አልገቡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያ መልካሙን ዜና በመጀመሪያ የሰሙት ባለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው የዕረፍት ቦታ አልገቡም፤ ሆኖም ወደዚያ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አንዳንዶች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ መንገድ ስለ ነበራቸው ቀድሞም የምሥራች የተሰበከላቸው ባለ መታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ |
መጽሐፍም፥ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፥ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፤” ብሎ አስቀድሞ ለአብርሃም ወንጌልን ሰበከለት።