Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከርስታቸው እነርሱን ለማጥፋት በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ አንተንም ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆነ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በቸነፈር እመታዋለሁ፤ እደመስሰዋለሁም፤ አንተን ግን ብርቱና ታላቅ ለሆነ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እነሆ፥ እኔ ቸነፈር አምጥቼ በመቅሠፍት እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነርሱ ይበልጥ ታላቅና ብርቱ ለሆነ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከርስታቸው አጠፋቸው ዘንድ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ አንተንም ከእነርሱ ለሚበዛና ለሚጠነክር ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 14:12
9 Referencias Cruzadas  

አሁንም ቁጣዬ በእነርሱ ላይ እንዲነድና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ።”


እንደገናም የጌታ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቁጠር” በማለት በእነርሱ ላይ አነሣሣው።


በመቅሠፍትም የሞተው ሰው ሀያ አራት ሺህ ነበረ።


እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት።


የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።


ጌታ ልትወርሳት ከምትገባባት ምድር ላይ እስኪያጠፋህ ድረስም ቀሣፊ በሽታ ይልክብሃል።


ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ፤ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሱ፥ በትእዛዜም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ። በዚህም ጊዜ፦ አጠፋቸው ዘንድ ቁጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios