ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በጌታ ስም እንዲህ ሲል ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በማቀዱ በሕይወቱ እንዲከፈል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ በበለጠም ይቅጣኝ!
ዕንባቆም 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሕዝቦችን ቆራርጠህ ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብዙ ሰዎች ነፍስ እንዲጠፋ አሢረሃል፤ በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ጥፋትን አምጥተሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተንኰልን ዐቅደህ ብዙ ሰዎችን በመግደል በቤትህ ኀፍረትን አምጥተሃል፤ ሕይወትህንም ለአደጋ አጋልጠሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ አሕዛብን አጥፍተሃልና ለቤትህ እፍረትን መክረሃል፥ በነፍስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል። |
ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በጌታ ስም እንዲህ ሲል ማለ፦ “አዶንያስ ይህን በማቀዱ በሕይወቱ እንዲከፈል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ በበለጠም ይቅጣኝ!
የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት።
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”
በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ ንጉሡ ጌታን አልፈራን? ወደ ጌታስ አልተማጠነምን? ጌታስ በእነርሱ ላይ የተናገረውን ክፉ ነገር አልተወምን? እኛም በነፍሳችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለን።”
ስለ ኃጢአታቸውም እርሱንና ዘሩን ባርያዎቹንም እቀጣለሁ፤ እነርሱም አልሰሙምና በእነርሱ ላይ የተናገርሁትን ክፉ ነገር ሁሉ በእነርሱና በኢየሩሳሌም በተቀመጡ፥ በይሁዳም ሰዎች ላይ አመጣለሁ።’ ”
አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ትሩፍ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ልጅንና ሕፃንን ከእናንተ ለማጥፋት ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?
ጌታ ከእንግዲህ ወዲህ በስምህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፤ ከአምላኮችህ ቤት ጣዖትንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የማትረባ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።
በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።
በኃጢአታቸው የተነሣ ሕይወታቸውን አሳልፈው ለሞት የሰጡትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፋችሁ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጓቸው፤ በጌታ ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።”