ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤
ዕንባቆም 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ ምን እንደሚለኝና በአቤቱታዬም ምን መልስ እንደምሰጥ ለማየት እጠባበቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፤ በምሽጉ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ ምን እንደሚለኝ፣ ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፥ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። |
ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤
እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤
በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ቃፊር ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ መቃረባቸውን አይቶ፥ “ሰዎች እየጋለቡ ሲመጡ አያለሁ!” ሲል የጥሪ ድምፅ አሰማ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ” አለው።
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
ይህንንም የምለው ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሆነ ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ኀያል ነው።