Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕንባቆም 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፤ በምሽጉ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ ምን እንደሚለኝ፣ ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ ምን እንደሚለኝና በአቤቱታዬም ምን መልስ እንደምሰጥ ለማየት እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፥ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዕንባቆም 2:1
23 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ላ​ካ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ቅን ያል​ሆ​ነን ነገር በስ​ውር አደ​ረጉ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመ​ሸ​ገች ከተማ ድረስ በከ​ፍ​ታ​ዎች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ።


ሰላ​ይም ያያ​ቸው ዘንድ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመ​ጡም የእ​ነ​ኢ​ዩን አቧራ አየ። “እነ​ሆም፥ አቧራ አያ​ለሁ” አለ። ኢዮ​ራ​ምም፥ “ይገ​ና​ኛ​ቸው ዘንድ አንድ ፈረ​ሰኛ ይሂድ፤ እር​ሱም፦ ሰላም ነውን? ይበ​ላ​ቸው” አለ።


የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!


ከባለ ዕዳዬ የም​ቀ​በ​ለው ሳይ​ኖር ቀድ​ጀው እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


በማ​ለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማ​ለዳ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፥ እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለ​ሁም።


አቤቱ፥ ከአ​ማ​ል​ክት የሚ​መ​ስ​ልህ የለም፥ እንደ ሥራ​ህም ያለ የለም።


የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤


ማዕ​ዱን አዘ​ጋጁ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እና​ንተ አለ​ቆች ሆይ፥ ተነሡ፤ ጋሻ​ው​ንም አዘ​ጋጁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “ፈጥ​ነህ ሂድ፤ ጕበ​ኛ​ንም አቁም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንም ይና​ገር፤ የሚ​ሰ​ማ​ው​ንም ያውራ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ የአ​ፌን ቃል ስማ፤ በቃ​ሌም ገሥ​ጻ​ቸው።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው።


እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አምላኬም ይሰማኛል።


ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም።


በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos