ዘፍጥረት 44:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ “የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል፣ እንዲሁም ብር በየስልቻቸው አፍ ክተተው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፤ “ለመጫን የሚችሉትን ያኽል በየስልቻዎቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘው፥ “የእነዚህ ሰዎች ዓይበቶቻቸው መያዝ የሚችሉትን ያህል እህል ሙላላቸው፤ የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው፤ |
በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ዮሴፍ ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቾቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደ ተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፥ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።
ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፥ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፤ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ ፍሪዳ ተጥሎ ምሳ ይዘጋጅ” አለው።