La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 36:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጋታም፥ ቄናዝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፎ፥ ጋዕታምና ቀናዝ ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኤልፋዝም ልጆች እንዚህ ናቸው፤ ቴማን አማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 36:11
7 Referencias Cruzadas  

የዔሳው ልጆች ስም ይህ ነው፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝ፥ የዔሳው ሚስት የባሴማት ልጅ ረዑኤል።


ቲምናዕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ቁባት ነበረች፥ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፥ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጆች እነዚህ ናቸው።


ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።


ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?


ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።