ዘፍጥረት 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴኬምም አባትዋንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፥ “በፊታችሁ ሞገስን ባገኝ የምትሉኝን እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴኬም ደግሞ የዲናን አባትና ወንድሞቿን እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ እንጂ የተጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴኬምም፥ በበኩሉ የዲናን አባትና ወንድሞችዋን እንዲህ አላቸው፤ “ሐሳቤን ብትፈጽሙልኝ የምትፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴኬምም አባቷንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፥ “በፊታችሁ ሞገስን በአገኝ የምትሉትን ሁሉ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴኬምም አባትዋንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፦ በፊታችሁ ሞገስን ባገኝ የምትሉኝን እሰጣለሁ። |
መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ።
ዔሳውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን” አለ። እርሱ ግን፥ “ይህ ለምንድን ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል” አለ።