ዘፍጥረት 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባክህ ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፥ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በልጆቹ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጕዞ ዐቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እባክህ ጌታዬ አንተ ቀድመህ ሂድ፤ እኔም በዝግታ እከተልሃለሁ፤ በእንስሶቹና በልጆቹ ዐቅም ልክ እየተራመድኩ በኤዶም እደርስብሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እንሄዳለን፤ በጎዳናም እንውላለን፤ ወደ ጌታችን ወደ ሴይር እስክንደርስም በሕፃናቱ ርምጃ መጠን እንሄዳለን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታዬ ከባሪያው ፊት ቀድሞ ይለፍ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በሕፃናቱ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ። |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት
እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ።
እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እንዳይወርሯቸው ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ትተዋቸው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥
አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።