La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ፣ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያዕቆብም እንዲህ አለ፤ “ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ጌታዬ ታውቃለህ፤ ለሚያጠቡት እንስሶች፥ ለግልገሎቻቸውና ለእንቦሶቻቸው መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ እንስሶቹ በሙሉ ያልቃሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካ​ሞች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ለህ፤ በጎ​ችና ላሞ​ችም ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያጠ​ባሉ፤ ሰዎ​ችም በአ​ንድ ወይም በሁ​ለት ቀን በች​ኮላ የነ​ዱ​አ​ቸው እንደ ሆነ ከብ​ቶቹ ሁሉ ይሞ​ታሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም አለው፦ ጌታዬ ሆይ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆን ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 33:13
10 Referencias Cruzadas  

እርሱም ተነሣና “እንግዲህ እንሂድ፥ እኔም በፊትህ እሄዳለሁ” አለ።


እባክህ ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፥ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በልጆቹ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ።”


ዳዊትም እንዲህ ብሏልና፦ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለጌታም የሚሠራው ቤት በአገሩ ሁሉ በስሙና በክብሩ እጅግ ታላቅና ዝነኛ ሊሆን ይገባል፤ እኔም ስለዚህ ዝግጅትን አደርጋለሁ።” ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ የግንባታ ቁሳቁስ አዘጋጀ።


ከሚያጠቡ በጎችም በኋላ፥ ባርያውን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ወሰደው።


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፥ የክፉ ሰው ርኅራኄ ግን ጭካኔ ነው።


መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።


እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው።