ዘፍጥረት 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፤ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ፤ ሰዎችም በአንድ ወይም በሁለት ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆነ ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ፣ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ያዕቆብም እንዲህ አለ፤ “ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ጌታዬ ታውቃለህ፤ ለሚያጠቡት እንስሶች፥ ለግልገሎቻቸውና ለእንቦሶቻቸው መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ለአንድ ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ እንስሶቹ በሙሉ ያልቃሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እርሱም አለው፦ ጌታዬ ሆይ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆን ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ። Ver Capítulo |