ዘፍጥረት 32:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ሌሊት ከዚያው ሰፈረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን አወጣ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው ዐደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለዔሳው እጅ መንሻ እነዚህን መረጠ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ዐደረ፤ በማግስቱም ካለው ነገር ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነገር መርጦ አዘጋጀ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት በዚያው አደረ። ለወንድሙ ለዔሳውም የሚወስደውን እጅ መንሻ አወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚይችም ሌሊት ከዚያው አደረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳ እጅ መንሻን አወጣ፤ |
ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ያዕቆብም አለ፥ “እንደዚህ አይሁን፥ ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ፥ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ፥ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፥ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።
የገዛ አገልጋዮችህን ጠይቅ፤ እነርሱም ይነግሩሃል። ስለዚህ እነዚህ ወጣቶቼ በፊትህ ሞገስ ያግኙ። አመጣጣችን በግብዣ ቀን በመሆኑ እባክህን ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት የምትችለውን ያህል ስጥ።’ ”