Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የሰው ስጦታ መንገዱን ታሰፋለታለች፥ በታላላቆችም ፊት ታገባዋለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስጦታ ለሰጪው መንገድን ይከፍትለታል፤ ወደ ትልልቆች ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 18:16
10 Referencias Cruzadas  

ብዙ ሰዎች ለጋሱን ያቈላምጣሉ፥ ስጦታ ለሚሰጥም ሁሉ ወዳጅ ነው።


ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።


ገንዘብ ባደረገው ፊት መማለጃ እንደ ተዋበ ዕንቁ ነው፥ ወደ ዞረበትም ስፍራ ሁሉ ሥራውን ያቀናል።


አገልጋይህም ለጌታዬ ያመጣችው ይህ ስጦታ አንተን ለሚከተሉ ጐልማሶች ይሰጥ።


ያዕቆብም አለ፥ “እንደዚህ አይሁን፥ ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ፥ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ፥ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።


‘እንዲሁም ባርያህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ እንድትሉት። እሱ ‘በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይቀበለኛል ፊቱንም አያለሁ’ ብሎ አስቧል።”


ስጦታ በስውር ቁጣን ታጠፋለች፥ የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቁጣን ታበርዳለች።


እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ በአህያ አስጭኖ፥ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።


ወደ ፍርድ አስቀድሞ የገባ ጻድቅ ይመስላል፥ ባልንጀራው ግን መጥቶ ይመረምረዋል።


ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios