በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ዘፍጥረት 32:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም፦ ‘በርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተንሣ እንድማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር። |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው እንዲህ አሉት፥ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፥ እርሱም ደግሞ ሊቀበልህ ይመጣል፥ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች” አሉ።
‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ ይህችንም ምድር ሁሉ እንደተናገርሁት ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘለዓለምም ይወርሱአታል’ ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባርያዎችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና እስራኤልን አስብ።”
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?