ዘፍጥረት 31:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ተቆጣ ላባንም ወቀሰው፥ ያዕቆብም ላባንም እንዲህ አለው፥ “ምን በደልሁህ? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ፥ ኃጢአቴስ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቈጣ፤ ላባንም እንዲህ ሲል ወቀሠው፤ “እስኪ ወንጀሌ ምንድን ነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኀጢአቴ ምን ቢሆን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ ሲል ላባን በቊጣ ቃል ተናገረው፤ “ታዲያ፥ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እስቲ ምን አጥፍቼ ነው እንዲህ የምታሳድደኝ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ተቈጣ፤ ላባንም ወቀሰው፤ ያዕቆብም መለሰ፤ ላባንም እንዲህ አለው፥ “የበደልሁህ በደል ምንድን ነው? ኀጢአቴስ ምንድን ነው? ይህን ያህል ያሳደድኸኝ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ተቆጣ ላባንም ወቀሰው ያዕቆብም መለሰ ላባንም እንዲህ አለው የበደልሁ በደል ምንድር ነው? ኃጢአቴስ ምንድር ነው ይህን ያህል ያሳደድኸኝ? |
እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።
አሁንም ዕቃዬን ሁሉ በረበርህ፥ የቤትህስ ሁሉ የሆነ ዕቃ ምን አገኘህ? እነርሱ በእኛ በሁለታችን መካከል ይፈርዱ ዘንድ በዘመዶቼና በዘመዶችህ ፊት አቅርበው።
የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።
ይህም ኤልሳዕን አስቆጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን “አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ” አለው።
ንዕማን ግን ተቆጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጉረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር!
ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”