ዘፍጥረት 31:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም35 ራሔልም አባቷን፣ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቈጣ፤ የወር አበባዬ መጥቶ ነው።” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖታቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 ራሔልም አባቷን “ጌታዬ በወር አበባዬ ምክንያት መነሣት ስላልቻልኩ ቅር አትሰኝብኝም” አለችው። ላባ በሁሉ ስፍራ ፈልጎ ጣዖቶቹን ማግኘት አልቻለም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 እርስዋም አባቷን፥ “ጌታዬ በፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ የአቀለልሁህ አይምሰልህ፤ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። ላባም የራሔልን ድንኳን በረበረ፤ ነገር ግን ጣዖቶቹን አላገኘም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 እርስዋም አባትዋን፦ በፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፤ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና አለችው። እርሱም ፈለገ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም። Ver Capítulo |