ዘፍጥረት 31:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “የፈጸምከው ምንድነው? እኔን አታልልከኝ፥ ልጆቼንስ እንደ ሰይፍ ምርኮኛ ለምን ወሰድካቸው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ምን ማድረግህ ነው? አታልለኸኛል፤ ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድሃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልከኝ? ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደ ተማረኩ ያኽል ይዘሃቸው ለምን ሄድክ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን አለው፥ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ በስውር የኰበለልህ? ልጆችንስ ሰርቀህ በሰይፍ እንደማረከ የወሰድኻቸው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ያዕቆብን አለው፦ ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ ከድተህ ኮበለልህ ልጆቼንም በሰይፍ እንደ ተማረኩ ዓይነት ነዳሃቸው። |
በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ሆና ተገኘች፥ ላባንም፦ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።
ላባም ያዕቆብን ደረሰበት፤ ያዕቆብም ድንኳኑን ኮረብታማው አገር ተክሎ ነበር፥ ላባም ከዘመዶቹ ጋር በገለዓድ ኮረብታማው አገር ድንኳኑን ተከለ።
ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”
ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።