ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ።
ዘፍጥረት 24:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብልንም በፊቱ አቀረበለት፥ እርሱ ግን፦ “ነገሬን እስክናገር ድረስ አልበላም” አለ። እርሱም፦ “ተናገር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰውየውም ማእድ ቀረበለት፤ እርሱ ግን፣ “የመጣሁበትን ጕዳይ ሳልናገር እህል አልቀምስም” አለ። ላባም፣ “ዕሺ፤ ተናገር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገበታ በቀረበ ጊዜ ሰውየው “የተላክሁበትን ጉዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም” አለ። ላባም “ይሁን ተናገር” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይበላም ዘንድ እንጀራን አቀረቡለት፤ እርሱ ግን “ነገሬን እስክናገር ደረስ አልበላም” አለ። እነርሱም “ተናገር” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብልንም በፊቱ አቀረበለት፤ እርሱ ግን፦ ነገሬን እስክናገር ድረስ አልበላም አለ። |
ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።
የሚያምኑም ጌቶች ያሉአቸው፥ ወንድሞች ስለ ሆኑ አይናቋቸው፤ ይልቁንስ ከበፊት ይልቅ ያገልግሏቸው ምክንያቱም በመልካም ሥራቸው የሚጠቀሙት አማኞችና ወዳጆቻቸው ናቸውና። እነዚህን ነገርች አስተምርና ምከር።