አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ዘፍጥረት 21:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፥ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አብርሃም፣ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም በመካከላቸው የስምምነት ውል አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሐላ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቤሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብረሃምም በጎችንና ላሞችን አምጥቶ ለአቤሜሌክ ሰጠው፤ ሁለቱም ቃል ኪዳን አደረጉ። |
አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።