ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
ዘፍጥረት 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ከተሞች ላይ እሳትና ዲን ከራሱ (ከእግዚአብሔር ዘንድ) ከሰማይ አዘነበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ |
ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ።
እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
ሰዶምና ገሞራ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ጎረቤቶቻቸው እንደ ተገለባበጡ፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ጎረቤቶቻቸውን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዲሁ ማንም ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
ኤፍሬም ሆይ! እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ጲቦይም እመለከትሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።
“ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለባበጣቸው፥ እንዲሁ ገለባበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና ሞዓብ እንደ ሰዶም፥ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ ይሆናሉ፥ አረም እንደ ዋጠው ስፍራና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘለዓለምም ይጠፋሉ፤ የሕዝቤም ትሩፍ ይበዘብዛቸዋል፥ ከወገኔም የተረፉት ይወርሱአቸዋል።
“የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሪቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና ጌታ ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ ዐመድም እንደ ሆነች፥ እንዳይዘራባት፥ እንዳይበቅልባትም፥ ማናቸውም ሣር እንዳይወጣባት፥ ጌታ በታላቅ ቁጣና መዓቱ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና ጺባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።