ኢዮብ 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወረደች፤ በጎችንና አገልጋዮችንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የመጀመሪያው መልእክተኛ ንግግሩን ገና ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጣና “በጎቹንና እረኞቹን በሙሉ መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ገደላቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እርሱም ገና ይህን ሲናገር ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፦ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎችህንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችህንም በላች፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው። Ver Capítulo |