ዘፍጥረት 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፥ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐሥራ አራተኛው ዓመት ኮሎዶጎምርና ከርሱ ጋራ የተባበሩት ነገሥታት ወጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፣ ዙዚምን በሃም፣ ኤሚማውያን በሴዊ ቂርያታይም፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አራተኛው ዓመት ከዶርላዖሜርና ከእርሱ ጋር የተባበሩት ነገሥታት ከነሠራዊቶቻቸው መጥተው ረፋያውያንን በዐስታሮት ቃርናይም፥ ዙዛውያንን በሃም፥ ኤማውያንን በሻዌ ቂርያታይም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎምርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይ፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፤ |
ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
የለመለመም እጅግም ያማረ መሰማሪያ አገኙ፥ ምድሪቱም ሰፊ ጸጥታም ያለላትና ሰላም የሰፈነባት ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛለችም፤ አምባይቱም አፍራለች ፈርሳለችም።
ከራፋያውያን ወገን የባሳን ንጉሥ ዖግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፥ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በራባት አለ፥ ቁመቱ ዘጠኝ ክንድ የጎኑም ስፋት አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
ከገለዓድም የቀረውን የዖግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ግዛት ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፥ ያቺ ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተጠራች።
ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”
በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ብቻ ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ ድል አድርጎ አስወጣቸው።
የገለዓድም እኩሌታ፥ በባሳንም ያሉት የዐግ መንግሥት ከተሞች፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበረ። እነዚህም ለማኪር ልጆች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ድርሻቸው ሆነ።
በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን ንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።