Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ ከሠላሳዎቹ አለቆች ሦስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንድ ቀን ከሠላሳዎቹ ጀግኖች ሦስቱ ወታደሮች ፍልስጥኤማውያን በራፋይም ሸለቆ ሰፍረው በነበረበት ጊዜ፥ ዳዊት በሚኖርበት በአዱላም ዋሻ አጠገብ ወዳለው አለት ሄዱ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከሠ​ላ​ሳ​ውም አለ​ቆች ሦስቱ ወር​ደው ዳዊት ወዳ​ለ​በት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶ​ላም ዋሻ መጡ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 11:15
11 Referencias Cruzadas  

ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ፍልስጥኤማውያን እንደገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


እርሱና ዳዊት በእርሻውም መካከል ጸንተው ቆሙ፤ ስፍራውንም አላስደፈሩም፥ ፍልስጥኤማውያንንም ገደሉ፤ ጌታም በታላቅ ድል አድራጊነት አዳናቸው።


ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኃያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ የሕዚኤል፥ ዮሐናን፥ ገድሮታዊው ዮዛባት፥


ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ አደጋ ጣሉ።


አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ፥ በራፋይም ሸለቆ እንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።


በማሬሻ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፤ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዱላም ይመጣል።


የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥


ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ፤


ዳዊት ከጋት ተነስቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ ሸሸ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ እርሱ ወዳለበት ወደዚያው ወረዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos