ዘፍጥረት 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክ እና ቲራስ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያፌት ልጆች፣ ጎሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሜሼኽ፣ ቴራስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያፌት ልጆች፦ ጎሜር፥ ማጎግ፥ ማዳይ፥ ያዋን፥ ቱባል፥ ሜሼክና፥ ቲራስ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። |
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።
ዓላማ ሆኖ እንዲያገለግልሽ፥ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሻ ደሴቶች የመጣ ሰማያዊና የወይን ጠጅ ነበር።
ሜሼክና ቱባል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሰይፍ ተገድለዋል።
በስተ ሰሜን ርቆ ከሚገኘው ስፍራህ አንተ፥ ከአንተም ጋር ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ ብዙ ሕዝብ፥ ታላቅ ጉባኤና ብርቱ ሠራዊት ጋር ሆነህ ትመጣለህ።
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥